የብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎትን ጀብድ የሚያሳየው “ንስሮቹ” ፊልም ተመረቀ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎትን ጀብድ የሚያሳየው “ንስሮቹ” ፊልም ተመርቋል።
ፊልሙን የመረቁት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ ታገሰ ጫፎ ናቸው።
የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ያዘጋጀውና በታምራት መኮንን ፊልም ፕሮዳክሽን የተሰራው ፊልሙ ፥ አገልግሎቱ የኢትዮጵያን ህልውና ለማስጠበቅ የሰራውን ሥራ በእውነተኛ ታሪክ ላይ ተመስርቶ የሚያሳይ ነው።
በእውነተኛ ታሪክ ላይ ተመስርቶ አገልግሎቱ የኢትዮጵያን ህልውና ለማስጠበቅ የሰራውን ስራ የሚያሳይ ነው።
የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ተመስገን ጥሩነህ እንደተናገሩት ÷ ፊልሙ የማድረግ አቅሙ በየጊዜው እየላቀ ያለ ተቋም እየተገነባ እንዳለ በጥበብ ለማሳየት ታልሞ የተሰራ ነው ።
ወዳጅ እንዲኮራ ጠላት እንዲፈራ ፤ ወዳጅ እንዲተማመን ጠላት እንዲመነምን መስራት ብቻ ሳይሆን የሰራነውን ማሳየት አለብንም ብለዋል።
የፊልሙ አጠቃላይ ስራ ከአንድ አመት በላይ እንደፈጀ ተገልጿል ።
በአልዓዛር ታደለ