Fana: At a Speed of Life!

የሶማሊያ ፕሬዚዳንት በኳታር የስራ ጉብኝት እያደረጉ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሐሰን ሼክ ሞሃሙድ በኳታር የስራ ጉብኝት እያደረጉ ነው፡፡
 
ፕሬዚዳንት ሐሰን ሼክ ሞሃሙድ ከኳታሩ ኤሚር ሼክ ታሚም ቢን ሃማድ አልታኒ በቀረበላቸው ግብዣ ለሁለት ቀናት የሥራ ጉብኝት ኳታር ዶሃ ገብተዋል፡፡
 
ፕሬዚዳንቱ ሃማድ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የኳታር ባህል ሚኒስትርን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የሀገሪቱ ባለሥልጣናት አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡
 
ፕሬዚዳንት ሐሰን ሼክ ሞሃሙድ በዶሃ ቆይታቸው ከኳታሩ ኤሚር ሼክ ታሚም ቢን ሀማድ አልታኒ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ እንደሚመክሩ ይጠበቃል፡፡
 
በተለይም ሀገራቱ በልማት፣ ሰላም እና ጸጥታ ዘርፎች ያላቸውን ትብብር ይበልጥ ማሳደግ በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ እንደሚመክሩ ተጠቁሟል፡፡
 
በኢኮኖሚ፣ በኢንቨስትመንት፣ በትምህርት እና ሌሎች ዘርፎች ላይ ባላቸው ትብብር ዙሪያ በትኩረት እንደሚወያዩም የፕሬዚዳንቱ ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.