Fana: At a Speed of Life!

ጃፓን ለኢትዮጵያ 5 ሺህ 700 ሜትሪክ ቶን ሩዝ ድጋፍ አደረገች

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጃፓን መንግስት ለኢትዮጵያ 5 ሺህ 700 ሜትሪክ ቶን ሩዝ ድጋፍ አድርጓል፡፡

ድጋፉ በኢትዮጵያ እና በጃፓን መንግስት መካከል ቀደም ሲል የተፈረመ የድጋፍ ስምምነት ሲሆን በዛሬው እለት ርክክብ ተደርጓል፡፡

የሩዝ ድጋፉ በገንዘብ ሚኒስቴር ዴኤታ ሰመሪታ ሰዋሰው እና በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ኢቶ ታካኮ መካከል ርክክብ ተደርጓል፡፡

ድጋፉ በኢትዮጵያ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት እና እየጨመረ የመጣውን የሩዝ ምርት ፍላጎት ለማስተካከል አስተዋፅዖ  ያደርጋል መባሉን የገንዘብ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

የተደረገው ድጋፍ በገንዘብ ሲተመን 300 ሚሊየን ብር እንደሚያወጣ ተጠቅሷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.