Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በአዲስ አበባ ለሚያስገነባው ቤተ-መንግስት የግንባታ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በአዲስ አበባ ለሚያስገነባው ቤተ- መንግስት ግንባታ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው፡፡
 
በመርሐ ግብሩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ የክልል እና የፌዴራል መንግስት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
 
የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ሀደ ሲንቄዎች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች መገኘታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
 
ቤተ መንግስቱ የኦሮሞን ሕዝብ ወግ፣ ባህል እና ታሪክ በሚያንጸባርቅ መልኩ እንደሚገነባ ተገልጿል፡፡
 
የግንባታ ሒደቱም በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ እንደሚጠናቀቅ በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ላይ ተጠቁሟል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.