Fana: At a Speed of Life!

የአምራች ኢንዱስትሪዎችን ምርታማነት በማሳደግ የኮሮና ቫይረስ ያስከተለውን ችግር ለመፍታት እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 16፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአምራች ኢንዱስትሪዎችን ምርታማነት በማሳደግ የኮሮና ቫይረስ ያስከተለውን ችግር ለመፍታት ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ገለጸ።

የኮሮና ቫይረስ መከሰትን ተከትሎ አምራች ኢንዱስትሪዎች ሰራተኛ እንዳያሰናብቱ፣ ምርት እንዳይቀንሱ እና ፋብሪካ እንዳይዘጉ ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል ተናግረዋል።

ቫይረሱ ያስከተለውን ችግር ለመፍታትም የሚያስፈልጉ ምርቶችን ለሚያመርቱ ኢንዱስትሪዎች የውጪ ምንዛሪ አቅርቦትን በማሻሻል በሙሉ አቅማቸው እንዲያመርቱ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑንም ነው የተናገሩት።

የሳሙና እና ዲተርጀንት ፋብሪካዎች ያለባቸውን የጥሬ እቃ ችግር ለመፍታት 100 ሚሊየን ዶላር ተመድቦ የሚያስፈልጋቸውን ጥሬ እቃ እንዲያስገቡ እየተደረገ መሆኑን ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

እንዲሁም በሀገር ውስጥ የሚገኙ 18 ሺህ 855 በላይ አነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች ከወረርሽኙ መከሰት ጋር ተያይዞ በሚገጥሟቸው የገበያ መቀዛቀዝና በሌሎች ችግሮች ምክንያት ከገበያ እንዳይወጡ የሚያስፈልጋቸው የድጋፍ ማዕቀፎች ተዘጋጅቷል መባሉን ከንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.