Fana: At a Speed of Life!

3ኛው የ“ላፕሴት” ፕሮጀክት የሚኒስትሮች ስብስባ በጁባ መካሄደ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ፣ ኬንያና ደቡብ ሱዳንን በትራንስፖርት የሚያስተሳስረው የ“ላፕሴት” ፕሮጀክት የሚኒስትሮች ስብስባ በጁባ መካሄደ ጀመረ፡፡

ስብሰባው “ፈጣን የ“ላፕሴት” ፕሮጀክት ትግበራ ለሰላም፣ ለእድገት፣ ለዘላቂ  ልማትና ለቀጣናዊ ትስስር” በሚል መሪ ቃል ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡

ከዛሬ ጀምሮ ለሶስት ቀናት የሚቆየው ስብሰባው የፕሮጀክቱን ትግበራ ለማፋጠን ያለመ ውጤታማ ሰነድ ይፀድቅበታል ተብሎ ይጠበቃል።

በኢፌዴሪ የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) የተመራው የኢትዮጵያ ልዑክም በስብሰባው እየተሳተፈ ይገኛል።

ከየሀገራቱ የተውጣጡ የንግድ ማህበረሰቦች፣ የልማት አጋሮች እና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን ማካተቱም ተገልጿል።

ስብሰባው በደቡብ ሱዳን  የትራንስፖርት ሚኒስቴር እና ከተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ነው።

የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) የላፕሴት ኘሮጀክት ራዕይን እውን ለማድረግ ኢትዮጵያ ያላትን ቁርጠኝነት በመግለፅ፥  የሶስቱን ሀገራት ኢኮኖሚያዊ ትብብር እና ቀጣናዊ ውህደት ለማሳደግ ያለውን ጠቀሜታ አንስተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.