የኮንስትራክሽን ኤክስፖ እና አውደ ርዕይ መካሄድ ጀመረ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኮንስትራክሽን ኤክስፖ እና አውደ ርዕይ በሚሊኒየም አዳራሽ መካሄድ ጀምሯል።
በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በተዘጋጀውና ዛሬን ጨምሮ ለሶስት ቀናት በሚቆየው ኤክስፖ ከ26 ሀገራት የተውጣጡ ኩባንያዎች ይሳተፋሉ ተብሏል፡፡
ኤክስፖው ለኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ዘርፍ እድገት ዓለም አቀፍ ተሞክሮ ለማግኘት፣ ለልምድ ልውውጥ፣ በዘርፉ የኢንቨስትመንት አማራጮችን ለማስተዋወቅ እንደሚያግዝ ተመላክቷል፡፡
ኤክስፖውን የከተማ እና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ከሚመለከታቸው የፌደራል ተቋማት እና በመሰል የኤክስፖ ዝግጅት ልምድ ካላቸው ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር በመተባበበር የተዘጋጀ ነው፡፡
በኤክስፖው ማስጀመሪያ ሥነስርዓት ላይ ሚኒስትሮች እና ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
በለይኩን አለም