የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከኮሎምቢያ ምክትል ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ

By Feven Bishaw

May 18, 2023

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 10 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከኮሎምቢያ ምክትል ፕሬዚዳንት ፍራንሲያ ማርኬዝ ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም የሁለቱን ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር አብረው እንደሚሰሩ አስታውቀዋል።

በተጨማሪም በተለያዩ ዘርፎች የትብብር ዕድሎችን ለማስፋት አብረን እንደሚሰሩም በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል።