Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ከላቲን አሜሪካና መካከለኛው እስያ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማሥፋት እየሠራች ነው – የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 10 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)ኢትዮጵያ ከላቲን አሜሪካና መካከለኛ እስያ ጋር ያላትን የግንኙነት አድማስ ለማስፋት ውጤታማ ሥራዎች እየሠራች መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

የሚኒስቴሩ ቃል-አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም በሰጡት መግለጫ ÷ ኢትዮጵያ ከኮሎምቢያና ፓኪስታን ጋር ያላትን የፖለቲካ ግንኙነት በዘርፈ ብዙ የትብብር መስኮችን ለማስቀጠል ዲፕሎማሲያዊ እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ ናቸው ብለዋል፡፡

የኮሎምቢያ ምክትል ፕሬዝዳንት ፍራንሲያ ኤሌና ማርኬዝ በኢትዮጵያ ለሁለት ቀናት የሥራ ጉብኝት እያደረጉ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ምክትል ምክትል ፕሬዚዳንቷ በቆይታቸው ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ፍሬያማ ውይይት እንዳደረጉ አምባሳደሩ ገልፀዋል።

በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ የተመራው ልዑክም ባሳለፍነው ሳምንት በፓኪስታን ቆይታ ማድረጉን አንስተዋል፡፡

በሀገራቱ መካከል የንግድ፣ ኢንቨስትመንት እና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት አዲስ ምዕራፍ ከፋች የሆኑ ዲኘሎማሲያዊ ተግባራት እንደተፈፀሙም ነው ያስታወቁት።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.