የሀገር ውስጥ ዜና

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የግብርና ሳይንስ አውደ ርዕይን ጎበኙ

By Mikias Ayele

May 18, 2023

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት “ከቤተ-ሙከራ ወደ አዝመራ” በሚል መሪ ቃል በሳይንስ ሙዚየም የተዘጋጀውን የግብርና ሳይንስ አውደ ርዕይ ጎብኝተዋል፡፡

አባላቶቹ ለሀገሪቱ የጀርባ አጥንት የሆነውን የግብርና ዘርፍ ለማዘመን እና የአርሶ አደሩን ህይወት ለማሻሻል የግብርና ሚኒስቴር እያከናወናቸው የሚገኙ ዘርፈ ብዙ ተግባራት የሚበረታቱ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡

አውደ ርዕዩ እስከ ግንቦት ወር መጨረሻ ድረስ የሚቆይ ሲሆን በግብርናው መስክ የተሰማሩ ከ70 በላይ የምርምርና ፈጠራ ስራዎች፣ ዲጅታላይዜሽን ፣ ግብርና እና የግብርና ፋይናንስ ላይ ያተኮሩ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች ለዕይታ ቀርበዋል።

በሳይንስ ሙዚየም የተሰናዳውን አውደ ርዕይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሚያዝያ 30 ቀን 2015 ዓ.ም መክፈታቸው ይታወሳል።

በምንተስኖት ሙሉጌታ