የሀገር ውስጥ ዜና

ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ ከኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ጋር ተወያዩ

By Mikias Ayele

May 18, 2023

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ  ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ ከኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ጋር በክልሉ እየተሰሩ ያሉ መንገዶችን በተመለከተ ተወያይተዋል።

ርዕሰ መስተደድሩ በውይይቱ እንደገለፁት÷ ከዚህ ቀደም ከኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደርና መንገዶቹን ከሚሰሩ ተቋራጮች ጋር በመሆን በክልሉ ለመንገድ ስራዎች እንዳይፋጠኑ እንቅፋት የሆኑ ቸግሮች ተለይተዋል።

በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረትም በክልሉ መንግስት መፈታት የነበረባቸው ችግሮች መፈታት መቻላቸውን አንስተዋል፡፡

የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር በክልሉና በፌዴራል መንግስት ድጋፍ እየተሰሩ ያሉ መንገዶች በፍጥነት ተጠናቀው ለህብረተሰቡ ክፍት እንዲሆኑ በትኩረት እንዲሰራ አሳስበዋል።

የክልሉ መንግስት የመንገዶቹ ግንባታ እስከሚጠናቀቅ በአስተዳደሩ የሚቀርቡ ትብብሮችን  በሃላፊነት ተቀብሎ  እንደሚሰራም ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን በክልሉ በፌዴራል መንግስት እየተሰሩ ያሉ የመንገድ ስራዎች የደረሱበትን ደረጃ ሪፖርት አቅርበው ውይይት መደረጉን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡