Fana: At a Speed of Life!

ከባድ የድካም ስሜት ምንድን ነው?

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 10 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከባድ የድካም ስሜት በአብዛኛው አልፎ አልፎ የሚከሰት ሲሆን አንዳንድ ሰዎች ላይ ደግሞ በተደጋጋሚ ይከሰታል፡፡

ነገር ግን ከባድ የድካም ስሜት በህክምናው አጠራር “ሚያልጅክ ኢንስፋሎሚየላይትስ” (ኤም ኢ/ሲኤፍ ኤስ ) ከሌሎቹ የድካም ስሜቶች የተለየ እንደሆነ የዘርፉ ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡

ይህንን የድካም ስሜት የተለየ የሚያደርገው የሚፈጥረው የድካም ስሜት እስከ ስድስት ወራት በተከታታይ ሊዘልቅ የሚችል እና የቀን ተቀን ስራን እንዳናከናውን የሚያውክ በመሆኑ ነው፡፡

ይህ ከፍተኛ የድካም ስሜት ያለበት ሰው የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በሚያደርግ ጊዜ በተለይ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ባደረገ በማግስቱ የድካም ስሜቱ ሊባባስ ይችላል ይላሉ የህክምና ባለሙያዎች፡፡

የድካም ስሜቱ በተደጋጋሚ የሚከሰት ሲሆን ሁልጊዜም በቂ እንቅልፍ ያላገኙ ያህል ሊሰማዎት ይችላል፡፡

በሌሊት ድንገት የመንቃት፣ ትኩረት የማጣት ችግር ፣ ቁጭ ብለው ወይም ተኝተው ሲነሱ የማዞር ስሜት፣ ልብ በፍጥነት መምታት፣ ለረዥም ጊዜ ሲቆሙ በጣም መድከም እና የባህሪ መቀያየር ሊያስከትልም ይችላል፡፡

ይህ ችግር ሁሉም ሰው ላይ ማለትም ከህጻናት እስከ አዋቂ እድሜ ክልል የሚከሰት ቢሆንም በአብዛኛው ጊዜ ግን በ40 እና 50 የእድሜ ክልል በሚገኙ ሴቶች ላይ እንደሚበረታ ነው የሚነገረው፡፡

ከመካከለኛ እስከ ከፍተኛ ስሜት ያለው ሲሆን በአማካይ ሲታይ ከአራቱ የዚህ ችግር ተጠቂዎች በአንዱ ላይ ከፍተኛ ደረጃ የደረሰ ድካም ሊሰማው ይችላል፡፡

ቀለል ያለ የድካም ስሜት ያለው ሰው ራሱን መቆጣጠር የሚችል ሲሆን መካከለኛ ስሜት የሚያስተናግደው የህመም ስሜት በእለት ተእለት እንቅስቃሴው ላይ እክል ሊፈጥርበት ይችላል።

አንድ ሰው በከፍተኛ ድካም መጠቃቱን የሚያሳዩ ምልክቶች

በሽታን የመከላከል አቅም ማነስ፣ የአቅም ማነስ፣ ከአዕምሮ ጋር የተያያዙ ችግሮች፣ የደም ግፊት እና የልብ ችግር፣ የዘረ መል ውቅር ችግር፣ በቀላሉ ለኢንፌክሽኖን የመጋለጥ፣ የኮርቲሶል መጠን ማነስ ይስተዋልበታል።

ከዚህ ችግር ለመላቀቅም የጤና ባለሙያ በማናገር በባለሙያው የሚሰጡ የተለያዩ ህክምናዎችን በመውሰድ፣ የተመጣጠነ ምግብ በመመገብ ፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በማድረግና የመሳሰሉትን ማድረግ ይመከራል።

ምንጭ፦ዌብ ኤምዲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.