Fana: At a Speed of Life!

በገበታ ለትውልድ ገቢ ማሰባሰብ ዙሪያ ከሚሲዮን መሪዎች ጋር ውይይት ተደረገ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 12 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና የዲያስፖራ አገልግሎት በገበታ ለትውልድ ገቢ ማሰባሰብ ዙሪያ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ከሚገኙ የኢትዮጵያ ሚሲዮን መሪዎች ጋር ውይይት ተደረገ።

 

በበይነ መረብ የተደረገውን ውይይት  የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ሚኒስትር  አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ መርተውታል።

 

በውይይቱም ገበታ ለትውልድን ለመደገፍ በሚሲዮኖች እየተከናወኑ ስለሚገኙ ስራዎች እና እየተገኙ ስላሉ ውጤቶች እንዲሁም በቀጣይ አቅጣጫዎች ዙሪያ ከአምባሳደሮች እና ሚሲዮን መሪዎች ጋር ምክክር እንደተደረገ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ መረጃ ያመለክታል።

 

ገበታ ለትውልድ በሃገር አቀፍ ደረጃ በተለያዩ አካባቢዎች የተመረጡ ስምንት የቱሪዝም መስህብ ስፍራዎችን ለማልማት የተቀረፀ የልማት ፕሮጀክት ነው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.