Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ክልል የምርጥ ዘርና የግብርና ግብዓት ለትግራይ ክልል ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 12 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል መንግስት እና ህዝብ ለትግራይ ክልል መልሶ ማቋቋሚያ ከ18 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የሰብል ምርጥ ዘርና የተለያዩ የእርሻ መሳሪያዎች ድጋፍ አበርክቷል።

 

ድጋፉን ለማስረከብ ወደ መቐለ ከተማ ያመራው የደቡብ ክልል ልዑክ 1 ሺህ 500 ኩንታል ምርጥ ዘር እና 3 ሺህ 600 የተለያዩ የእርሻ መሳሪዎችን ለትግራይ ክልል ግብርና ቢሮ ኢያሱ አብርሃ (ዶ/ር) አስረክበዋል።

 

የደቡብ ክልል መንግስትን በመወከል ድጋፉን ያስረከቡት አቶ አለምይርጋ ወ/ስላሴ በዚሁ ወቅት እንደገለፁት ድጋፉ ችግሮችን በጋራ በመደጋገፍ ለማለፍ የተደረገ ነው።

 

ለትግራይ ክልል ህዝብና መንግስት አለኝታነትን ለመግለፅ  የተደረገ ድጋፍ መሆኑን በመጥቀስም፥ የመረዳዳት ባህልን ለማጎልበት እንደሚጠቅም ገልፀዋል።

 

በቀጣይም የደቡብ ክልል መንግስትና ህዝብ ከትግራይ ክልል መንግስትና ህዝብ ጎን በመቆም ድጋፉን እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

 

የትግራይ ክልል ግብርና የተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ኢያሱ አብርሃ (ዶ/ር) በበኩላቸው፥ ከዚህ ቀደም በተፈጠረው ግጭት ሳቢያ በክልሉ የግብርና ግብዓትና የምርጥ ዘር እጥረት መኖሩን ጠቅሰዋል።

 

የተበረከተው ድጋፍ በክልሉ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ጉልህ ድርሻ ይኖረዋል ማለታቸውን የደቡብ ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል።

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.