Fana: At a Speed of Life!

የሐይማኖት አባቶች የግብርና ሳይንስ አውደርዕይን ጎበኙ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 12 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከተለያዩ የሐይማኖት ተቋማት የተውጣጡ አባቶች በሳንይንስ ሙዚየም በመገኘት የግብርና ሳይንስ አውደርዕይን ጎብኝተዋል።

 

የሐይማኖት አባቶች በጉብኝታቸው በተለያዩ የግብርና ዘርፎች  እርሻ ልማት፣ ተፈጥሮ ሀብት ልማት እና እንስሳት ሀብት ልማት ሳይንስ ያፈራቸውን ምርቶችንና ቴክኖሎጂዎችን ተመልክተዋል።

 

በሌላ በኩል ከተለያዩ ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ ተማሪዎችም በሳይንስ ሙዚየም የተዘጋጀውን የግብርና ሳይንስ አውደርዕይ በዛሬው ዕለት እየጎበኙ እንደሚገኝ ከግብርና ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.