Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና ቻይና በአየር ንብረት ለውጥና በአካባቢ ጥበቃ ዘርፍ በጋራ ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸዉ ገለፁ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 12 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያና ቻይና በአየር ንብረት ለውጥና በአካባቢ ጥበቃ ዘርፍ በጋራ ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸዉ ገለፁ፡፡

የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዴኤታ  ሳንዶካን ደበበ ከቻይና የኢኮሎጂና የአካባቢ ጥበቃ ሚኒስቴር ልዑካን ጋር ተወያይተዋል።

በውይይቱ  አቶ ሳንዶካን እንደተናገሩት÷ ኢትዮጵያና ቻይና በአለምአቀፍ አየር ንብረት ለዉጥ ጉዳዮች ፣ በደቡብ ደቡብ ትብብር እና በሌሎች ኢኮኖሚያዊ ማህበራዊና ፖለቲካዊ መስኮች ላይ በርካታ ተግባራትን እያከናወኑ ያሉ ሀገራት መሆናቸዉን  አንሰተዋል፡፡

የአዲስ አበባን የወንዝ ዳር ልማቶች ጨምሮ ቻይና በኢትዮጵያ በግንባታዉ ዘርፍ ያላትን ተሳትፎ  ሚኒስትር ዴኤታዉ አድንቀዋል፡፡

ኢትዮጵያ  ከተፈጥሮ ጋር የተያያዙ አደጋዎች ዋጋ እያስከፈሏት መሆኑን ያነሱት  አቶ ሳንዶካን  ይህንን ለመከላከል   የረጅም ጊዜ ዝቅተኛ የካርበን ልቀትና ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ልማት ስትራቴጂን ተግባራዊ ማድረጓን  አብራርተዋል፡፡

እነዚህ ተግባራት ከፍተኛ ትብብርና ፋይናንስ የሚጠይቁ በመሆናቸዉ ቻይና ለዚህ ተገባር  ድጋፍ እንድታደርግ መጠየቃቸውን ከፕላንና ልማት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የቻይና የኢኮሎጂና የአየር ንብርት ለውጥ ሚኒስቴር የልዑካን ቡድን አባላት መሪና የአለማቀፍ ትብብር ሃላፊዋ  ዙሁ ጉዎሚን(ዶ/ር) በበኩላቸው÷ የኢትዮጵያን የአረንጓዴ አሻራ ተግባርና ዉጤት እንደሚያደንቁ  ገልፀው ሀገሪቱ ያላትን አረንጓዴ ልማትና አረንጓዴ ብልጽግና የማረጋገጥ ፍላጎት እንድንገነዘብ አስችሎናል ብለዋል፡፡

የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት በተግባር የተረጋገጠ እንዲሆን ቻይና ትፈልጋለች ያሉት ሃላፊዋ በቀጣይም የግንኙነታችን ፍሬ የሆኑ በርካታ ውጤቶችን በጋራ እናስመዘግባን ብለዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.