Fana: At a Speed of Life!

የአማራ ክልል የመሪዎች ኮንፈረንስ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መክሮ መግባባት ላይ በመድረስ ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 12 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል የመሪዎች ኮንፈረንስ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መክሮ መግባባት ላይ በመድረስ ተጠናቀቀ፡፡

የክልሉ መንግሥት ለቀናት ሲካሄድ የነበረው ኮንፈረንስ መጠናቀቅን ተከትሎ የአቋም መግለጫ አውጥቷል።

በክልሉ እየታዩ ያሉ  ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ እና  ማኅበራዊ ችግሮችን መገምገሙን መግለጫው አመልክቷል።

ከለውጡ ወዲህ ከፍተኛ የሆኑ ሥራዎች መሠረታቸውን በማንሳት፥ በለውጡ ዓመታት በርካታ ድሎች መገኘተቻውንም ጠቅሷል።

በለውጡ ሂደቶች በርካታ ችግሮች ማጋጠማቸውን ማንሳቱንም አሚኮ ዘግቧል ።

ሕዝቡ ሦስት አሥርት ዓመታት የታገለባቸውን የማንነት እና የወሰን ጥያቄዎች፣ የተሳሳተ ትርክት ትግል፣ ፍትሐዊ ተጠቃሚነት ማስፈን ላይ ትግል መደረጉን ነው ያስታወቀው።

“የአማራ ሕዝብ ጥያቄዎች ትክክለኛ እና ተገቢ ቢሆኑም በርካታ ፈተናዎች ገጥመውታል” ሲልም ነው ያመላከተው።

የአማራ ሕዝብ በኢትዮጵያዊነት ልዕልና የቆመ እና ጥያቄዎችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የሚጥር መሆኑንም አንስቷል።

ባለፉት ዓመታት በተሠሩ ሥራዎች ለዓመታት የቆዩ የሕዝብ ጥያቄዎች የሚፈቱበት መደላድል መፈጠሩም ተመላክቷል።

በኮንፈረንሱ እንደ ሕዝብ ያጋጠሙ ፈተናዎችን እና ድሎችን ገምግሟል ነው የተባለው።

የአማራ ክልል ችግሮችን መለየቱን  እና ለተፈፃሚነታቸው መግባባት ላይ መድረሱን መግለጫው አስታውቋል።

ኮንፈረንሱ በበርካታ ጉዳዮች ከተወያየ በኋላ ባለ ዘጠኝ ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ነው የተጠናቀቀው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.