Fana: At a Speed of Life!

ከተማ አቀፍ የማርሻል አርት ስፖርታዊ ፌስቲቫል ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ15ሺህ በላይ ስፖርተኞች የተሳተፉበት የማርሻል አርት ፌስቲቫል በአዲስ አበባ በመስቀል አደባባይ ተካሂዷል።
መርሐ ግብሩ “የማርሻል አርት ስፖርት ለከተማችን ሰላም እና ውጤታማ ትውልድ ግንባታ” በሚል መሪ ቃል ነው የተካሄደው፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች ስፖርት ቢሮ ባዘጋጀው የመጀመሪያ ከተማ አቀፍ የማርሻል አርት ፌስቲቫል ላይ የተለያዩ ስፖርታዊ ትርዒቶች መቅረባቸውን የቢሮው መረጃ ያመላክታል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ÷ማርሻል አርት ስፖርት ጥበብና እውቀት በማቀናጀት የሚካሄድ ስፖርት በመሆኑ ስፖርቱን ከማስፋፋት እና ተተኪዎችን ከማፍራት በተጨማሪ ለሰላም፣ አንድነት፣ ለትውልድ ግንባታ ልንጠቀምበት ይገባል ብለዋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.