የሀገር ውስጥ ዜና

በመዲናዋ በትራፊክ አደጋ የ2 ሰዎች ሕይወት አለፈ

By Alemayehu Geremew

May 21, 2023

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)በአዲስ አበባ ንፋስ ሥልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሁለት ሰዎች ሕይወት አለፈ።

የትራፊክ አደጋው የደረሰው በወረዳ 11 ልዩ ሥሙ አትክልት ተራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ መሆኑን የወረዳው ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

ሕይወታቸውን ካጡት ሁለት ሰዎች በተጨማሪ በሌሎች ሁለት ሰዎች ላይ ደግሞ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱንና በህክምና ክትትል ላይ እንደሚገኙም ተገልጿል፡፡