የሀገር ውስጥ ዜና

የኢትዮጵያን የግብርና ምርት ወጪ ንግድ በጂቡቲ በኩል ማቀላጠፍ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ተመከረ

By Alemayehu Geremew

May 21, 2023

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የኢትዮጵያን የግብርና ምርት ወጪ ንግድ በጂቡቲ በኩል ማቀላጠፍ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ምክክር ተካሄደ፡፡

በጉዳዩ ላይ የኢፌዴሪ የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ሶፊያ ካሳ (ዶ/ር) እና በጂቡቲ የዶራሌ ወደብ ዋና ሥራ አሥፈፃሚ ጃማ ኢብራሂም ተገናኝተው መክረዋል፡፡

በሁለቱ ወገኖች መካከል የተካሄደው ውይይት ፍሬያማ እንደነበረ ሚኒስትሯ መግለጻቸውን በጂቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ተነስተው በዋና የትኩረት ነጥቦች ላይ የተሻሻለ አሠራር ለመዘርጋት መስማማታቸውም ተጠቁሟል፡፡