አዲስ አበባ፣ ግንቦት 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ሚዛን ዓለም የ10 ሺህ ሜትር የሩጫ ውድድር በአሸናፊነት አጠናቃለች፡፡
አትሌቷ በለንደን ’’ኮንቲነንታል ቱር’’ ላይ በተደረገው የ10 ሺህ ሜትር የሩጫ ውድድር ከ30 ደቂቃ በታች በመግባት በታሪክ 12ኛዋ እንስት ሆናለች፡፡
በዚህ ውድድር ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ሚዛን ዓለም 29 ደቂቃ 58 ሰከንድ 70ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ውጤት ነው ውድድሯን ያጠናቀቀችው፡፡
ይህም ታሪክ የማይረሳው የኢትዮጵያ ድል ነው ሲሉ የዓለም አትሌቲክስ እና ሌሎች መገናኛ ብዙሃን አሞካሽተውታል፡፡
#Ethiopia #athletics #victory
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!