Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በዓለም የሚቲዎሮሎጂ ድርጅት ጉባዔ ላይ እየተሳተፈች ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 19ኛው የዓለም የሚቲዎሮሎጂ ድርጅት ጉባዔ በስዊዘርላንድ ጄኔቭ መካሄድ ጀምሯል፡፡

በጉባዔው በሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ፈጠነ ተሾመ እና በውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዴኤታ  አብርሃ አዱኛ (ዶ/ር) የተመራ ልዑል እየተሳተፈ ይገኛል፡፡

በመድረኩ የዓለም ሚቲዎሮሎጂ ድርጅት ዋና ፀሃፊ፣ የድርጅት ፕሬዚዳንት እና ም/ ፕሬዚዳንቶች፣ የቴክኒካል ኮሚሽን ፕሬዚዳንቶች፣ የስራ አስፈጻሚ ም/ቤት አባላት ምርጫን ጨምሮ የተለያዩ ውሳኔዎች እንደሚካሄዱ ይጠበቃል፡፡

በተጨማሪም በዓለም አቀፍ ደረጃ ቀልጣፋና ጥራት ያለው የአየር ሁኔታና ጸባይ አገልግሎት መስጠት የሚስችሉ ውሳኔዎች እንደሚተላለፉ ተጠቁሟል፡፡

በሌላ በኩል በዓለም ሚቲዎሮሎጂ ድርጅት ማሻሻዎች ዙሪያ የአመራሩን አቅም ማጎልበት የሚያስችሉ ውይይቶች እና ውሳኔዎች እንደሚተላለፉም የኢንስቲትዩቱ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.