Fana: At a Speed of Life!

የጋራ የሰላምና የልማት ትብብር ቻርተር ላይ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰላም ሚኒስቴር በአማራ እና አፋር ክልሎች መካከል ቋሚ የመንግስታት ግንኙነት እንዲኖር የሚያስችል የጋራ የሰላምና የልማት ትብብር ቻርተር ላይ ውይይት አካሂዷል፡፡

የጋራ ሰላምና የልማት ትብብሩ ዓላማ ዘላቂ ሰላም፣ልማትና ዋስትና ያለው ዴሞክራሲን ለመገንባት በሚደረገው ጥረት በተቀናጀ መንገድ የጋራና የተናጠል አቅሞችን አስተባብሮ የላቀ አቅምን በመፍጠር የክልሎቹን ህዝቦች የጋራ ተጠቃሚነትን ማፋጠን ነው ተብሏል፡፡

በተጨማሪም ትስስራቸውን ማጎልበት እና የፌዴራል ስርዓቱን ማጠናከር እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡

የትብብር ስምምነት ቻርተሩ በሁለቱም ክልሎች ሕዝቦች መካከል የቆየውን ወንድማማችነት ለማጠናከርና በክልሎቹ አዋሳኝ አካባቢዎች በሚኖሩ ማህበረሰቦች መካከል አልፎ አልፎ የሚስተዋሉ ግጭቶችን በጋራ ከመፍታት ባለፈ የህብረተሰቡን የልማት ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የሚያስችል እንደሆነም ተመላክቷል፡፡

በውይይይቱ የሁለቱም ክልሎች ርዕሳነ መስተዳድር ተወካዮች፣ የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ሀላፊዎችና የሰላም ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራረሮች  መገኘታቸውን የሰላም ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.