Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ የዓረብ ሊግ በሕዳሴ ግድብ ላይ ያሳለፈውን የውሳኔ ሃሳብ እንደማትቀበል ገለጸች

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ÷የዓረብ ሊግ በሕዳሴ ግድብ ላይ ያሳለፈው የውሳኔ ሃሳብ እንደማትቀበለው አስታውቃለች፡፡
 
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ÷በቅርቡ የተካሄደው የዓረብ ሊግ የመሪዎች ጉባኤ ያሳለፈው የውሳኔ ሀሳብ የኢትዮጵያን መንግስት እንዳሳዘነ ገልጿል፡፡
 
ውሳኔው በተለይም በግድቡ ዙሪያ ያለውን አለመግባባት በሰላማዊ ድርድር አንዲፈታ እየሰሩ ያሉትን የአፍሪካ ህብረትን እና አባል ሀገራትን ሚና የሚያኮስስ ነው ሲል አብራርቷል፡፡
 
የውሳኔ ሃሳቡ ታሪክን ከሚጋራው የአፍሪካ እና የዓረብ ሀገራት ግንኙነት በተቃራኒ የተወሰነ ውሳኔ መሆኑንም አስገንዝቧል፡፡፡
 
በሊጉ የተላለፈው የውሳኔ ሃሳብ የግብጽን የናይል ወንዝ ፍትሃዊ ያልሆነ አጠቃቀም የሚደግፍ መሆኑንም አጽንኦት ሰጥቷል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.