በደሴ የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ተጀመረ
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 16፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በደሴ ከተማ የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ተጀመረ።
ዛሬ አገልግሎት መስጠት የጀመረው የኮሮና ቫይረስ መመርመሪያ መሳሪያ በቀን በአማካይ 300 ሰዎችን መመርመር እንደሚያስችል የአማራ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ደሴ ቅርንጫፍ አስታውቋል።
የቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ አሰፋ ምሳዬ እንደገለጹት፥ አስፈላጊውን የቅድመ ዝግጅት ስራዎች በማጠናቀቅ የመመርመሪያ ማሽኑ ዛሬ በደሴ ጤና ጣቢያ አገልግሎት እንዲጀምር ተደርጓል።
የመመርመሪያ መሳሪያው ደሴ ከተማ አስተዳደርን ጨምሮ ደቡብ ወሎ ዞንና ለኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን አገልግሎት እንደሚሰጥ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።