Fana: At a Speed of Life!

ቻይና የኮምፒውተር ቁሶች ከአሜሪካው “ማይክሮን” እንዳይገቡ አገደች

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካውን የኮምፒውተር ቁሶች አምራች “ማይክሮን” ምርቶች ወደ ሀገሯ እንዳይገቡ ቻይና አገደች፡፡

በተለይ በኩባንያው የሚመረቱ የኮምፒውተር “ሜሞሪ ካርዶች” ለብሔራዊ ደኅንነቷ ሥጋት መሆናቸውን ጠቁማ ማገዷን የዘገበው አናዱሉ ነው፡፡

በቻይና ከግንኙነት መስመሮች ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ቴክኖሎጂዎች የሚጠቀሙ መሠረተ-ልማቶች ከተጠቀሰው የአሜሪካ ኩባንያ ምርት እንዳይገዙ በጥብቅ አሳስባለች፡፡

የቻይና የሳይበር ስፔስ አስተዳደር የመገናኛ ደኅንነት ቢሮ በጉዳዩ ላይ ክትትል አድርጎ የደኅንነት ሥጋት መሆናቸውን እንደደረሰበትም አስታውቋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.