የሀገር ውስጥ ዜና

ኢቲሳላት በኢትዮጵያ በቴሌኮም ዘርፍ የመሰማራት ፍላጎት እንዳለው አስታወቀ

By Melaku Gedif

May 23, 2023

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 15 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶቹ ኢቲሳላት በኢትዮጵያ በቴሌኮም ዘርፍ የመሰማራት ፍላጎት እንዳለው አስታወቀ።

የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) ከኢቲሳላት ዋና ስራ አስፈጻሚ ሃቲም ዶዊደር ጋር በበይነ መረብ ተወያይተዋል።

በዚህ ወቅትም ዋና ስራ አስፈጻሚው ኩባንያው በኢትዮጵያ በቴሌኮም ዘርፍ የመሰማራት ፍላጎት እንዳለው ገልጸዋል።

በተጨማሪም በዘርፉ ያሉትን እድሎች ለማየት ከኢትዮጵያ መንግስት እና ከዘርፉ ተዋናዮች ጋር ለመስራት ፍላጎት እንዳለው መናገራቸውን የገንዘብ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

በውይይታቸው ወቅት በቀጣዮቹ ሳምንታት በኢትዮጵያ ተገናኝተው ለመምከር መስማማታቸውም ታውቋል።