Fana: At a Speed of Life!

ከ209 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ209 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መያዛቸውን የጉምሩክ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

ኮሚሽኑ ከግንቦት 4 እስከ ግንቦት 10 ቀን  2015 ዓ.ም ባደረገው  ክትትል ነው 209 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ የኮንትሮባንድ እቃዎች የተያዙት፡፡

በቁጥጥር ስር ከዋሉት  ዕቃዎች መካከል አልባሳት፣ ነዳጅ፣ የቁም እንስሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ቡና፣ መድሃኒት፣ ተሽከርካሪዎች፣ የመዋቢያ እቃዎች፣ አደንዛዥ ዕጾች እና ሌሎች ዕቃዎች  ይገኙበታል፡፡

የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ በጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞች፣ በፌዴራል ፖሊስ፣ በብርበራና ጥቆማ የተያዙ መሆናቸውን የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹን ሲያዘዋውሩ የተገኙ 11 ግለሰቦች እና ዘጠኝ ተሽከርካሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውም ተጠቁሟል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.