Fana: At a Speed of Life!

ጃፓን “ኔቶ”ን የመቀላቀል ዕቅድ የላትም – ፉሚዮ ኪሺዳ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጃፓን የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል-ኪዳን ድርጅት “ኔቶ”ን የመቀላቀል ዕቅድ እንደሌላት የሀገሪቷ ጠቅላይ ሚኒስትር ፉሚዮ ኪሺዳ አስታወቁ፡፡

ፉሚዮ ጃፓን በማናቸውም መንገዶች አሜሪካ መራሹን የጦር ቃል-ኪዳን ድርጅት አትቀላቀልም ሲሉ አቋማቸውን ያስታወቁት በዛሬው ዕለት በተካሄደው የሀገሪቷ ፓርላማ ስብሰባ ላይ ነው፡፡

አሁን የተሰማው የጠቅላይ ሚኒስትሩ አቋም በአሜሪካ የጃፓን አምባሳደር የሆኑት ኮጂ ቶሚታ በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ ከሰጡት መግለጫ ጋር የማይጣጣም መሆኑን አር ቲ ሬውተርስን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል፡፡

በወቅቱ አምባሳደሩ በእስያ የመጀመሪያ ይሆናል ያሉትን የ”ኔቶ” ጽኅፈት ቤት በቶኪዮ ለመክፈት ጃፓን እየሰራች መሆኑን ጠቁመው ነበር፡፡

የጦር ቃል ኪዳን ድርጅቱም በሕንድ-ፓሲፊክ ቀጣና የመወከል ፍላጎት እንዳለው አልሸሸገም፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ፉሚዮ ÷ የጦር ቃል-ኪዳን ድርጅቱ ሥራዎቹን ለማሳለጥ ያመቸው ዘንድ በጃፓኗ ቶኪዮ ቢሮ ለመክፈት መጠየቁን አረጋግጠዋል፡፡

ሀገራቸው ግን ይሆናልም ፣ አይሆንምም የሚል ምላሽ አልሰጠችም ነው ያሉት፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.