Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት አ.ማ የጭነት ተሽከርካሪዎችን ከጅቡቲ አዲስ አበባ ማጓጓዝ ጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 16 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር በኩል ለመጀመሪያ ጊዜ የተጓጓዙ 63 የጭነት ተሽከርካሪዎች አዲስ አበባ ገብተዋል።
 
አክሲዮን ማህበሩ ከዚህ ቀደም መደበኛ ተሽከርካሪዎችንና የቤት አውቶሞቢሎችን ብቻ ሲያጓጉዝ መቆየቱ ይታወሳል።
 
በዛሬው ዕለት ደግሞ የጭነት ተሽከርካሪዎችን ከጅቡቲ ወደብ ወደ ሀገር ውስጥ ማጓጓዝ መጀመሩን ገልጿል።
 
የኢትዮ ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር ዋና ስራ አስፈጻሚ አብዲ ዘነበ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት÷ የኢትዮ- ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎቱን በማስፋት ላይ ይገኛል።
 
በዚህም የወጪ ገቢ የጭነት አገልግሎትን በባቡር ትራንስፖርት የማሳለጥ ስራ በስፋት መጀመሩን በማንሳት÷ ዛሬ ወደ ሀገር ውስጥ ተጓጉዘው የገቡት የጭነት ተሽከርካሪዎችም የዚሁ ተግባር ማሳያ ናቸው ብለዋል።
 
የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ ደንጌ ቦሩ በበኩላቸው÷በሀገሪቷ የኢኮኖሚ እድገት ውስጥ የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ዘርፍ ጉልህ ሚና እንዳለው መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.