Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በኢትዮጵያ የ ተ. መ. ድ. ዋና ተጠሪና የሰብአዊ ድጋፍ ዋና  አስተባባሪ ዶ/ር ካትሪን ሶዚ ጋር ተወያዩ

 

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 16፣2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በኢትዮጵያ የ ተ. መ. ድ. ዋና ተጠሪና የሰብአዊ ድጋፍ ዋና  አስተባባሪ ዶ/ር ካትሪን ሶዚ ጋር ተወያዩ፡፡

አምባሳደር ምስጋኑ በውይይታቸው÷ ኢትዮጵያ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና ልዩ ኤጀንሲዎች ጋር በቅርበት ለመስራት ያላትን ፍላጎት ገልጸዋል።

አስተባባሪዋ ዶክተር ካትሪን ሱዚ በኢትዮጵያ በተፈጠሩ አስቸጋሪ ጊዜያቶች የሰብአዊ አገልግሎት ተደራሽ በማድረግ ረገድ ላሳዩት ተነሳሽነት እና በሀገሪቱ የሰላም ግንባታ ሂደት ተቋማቸው ላደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ዶክተር ካትሪን ሱዚ በበኩላቸው÷ የሰብዓዊ ዕርዳታዎችን ተደራሽ ለማድረግ የኢትዮጵያ መንግስት ያሳየውን ትብብርና የፈጠረውን ምቹ ሁኔታ አድንቀዋል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኢትዮጵያ ዘላቂ የልማት ግቦቿን እንድታሳካ ድጋፍ ማድረጉን ይቀጥላል ሲሉ አስተባባሪዋ መናገራቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.