Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል 3 ሺህ 330 የባዮ ጋዝ ማብላያ መገንባቱ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ባለፉት ዘጠኝ ወራት 3 ሺህ 330 የባዮ ጋዝ ማብላያዎችን በመገንባት አርሶ አደሩን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን የክልሉ ውሃና ኢነርጂ ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮ ሃላፊው ማማሩ አያሌው (ዶ/ር) በሰጡት መግለጫ እንደገለጹት÷ የባዮ ጋዝ ማብላያ መገንባት ለሃይል አቅርቦት፣ ለግብርና ምርታማነትና ሌሎች ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎች አሉት።

በመሆኑም በክልሉ ለባዮ ጋዝ ግንባታ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ አርሶ አደሩን ተጠቃሚ ለማድረግ በ125 ወረዳዎች የግንባታ ሥራ ሲከናወን ቆይቷል መባሉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.