Fana: At a Speed of Life!

ዘመን ባንክ ከ1 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በላይ ያስገነባው የዋና መስሪያ ቤት ህንጻ ቅዳሜ ይመረቃል

 

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዘመን ባንክ ያስገነባው አዲስ የዋና መስሪያ ቤት ህንጻ የፊታችን ቅዳሜ ይመረቃል።

የባንኩ ቦርድ ሊቀመንበር አቶ ኤርሚያስ እሸቱ ዛሬ በሰጡት መግለጫ፥ ዘመን ባንክ ዘመኑን የዋጁ ቴክኖሎጅዎችን በመጠቀም ለደንበኞች ቀልጣፋና አስተማማኝ አገልግሎት እየሰጠ ነው ብለዋል።

ባንኩ ያስገነባው የዋና መስሪያ ቤት ህንጻም የፊታችን ቅዳሜ ይመረቃል ነው ያሉት።

የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ህንጻም ለከተማዋ ልዩ ድምቀት ከመሆኑ ባሻገር ባንኩ የደረሰበትን ከፍታ የሚገልጽ መሆኑን ጠቁመዋል።

ባንኩ ከ15 ዓመት በፊት በ87 ሚሊየን ብር ካፒታል የተመሠረተ ሲሆን፥ አሁን ላይ 100 ቅርንጫፎች እንዳሉት ተናግረዋል።

ዘመን ባንክ ባለፈው የፈረንጆቹ 2022 ከታክስ በፊት 2 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር በላይ ያተረፈ ሲሆን፥ ጠቅላላ ሃብቱ 40 ቢሊየን ብር መድረሱም ነው የተገለጸው።

ቅዳሜ የሚመረቀው ህንጻ 36 ወለል ያለው ሲሆን፥ ከ1 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ ነው የተገነባው።

በሜሮን ሙሉጌታ እና መላኩ ገድፍ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.