ኢንተርናሽናል አርቢትር ባምላክ ተሰማ የአፍሪካ ሻምፒንስ ሊግ የፍጻሜ ጨዋታን በዋና ዳኛነት ይመራሉ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢንተርናሽናል አርቢትር ባምላክ ተሰማ በአፍሪካ ሻምዮፒንስሊግ ፍፃሜ አል አህሊ ከዋይዳድ ካዛብላንካ የሚያደርጉትን የፍጻሜ ጨዋታ በዋና ዳኛነት እንደሚመሩ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) አስታውቋል፡፡
የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ በፈረንጆቹ የፊታችን ሰኔ 4 ቀን ሲደረግ አል አህሊ ዋይዳድ ካዛብላንካን በሞሃመድ 5ኛ ስታዲየም ያስተናግዳል፡፡
የመልሱ ጨዋታ ደግሞ ሰኔ 11 የሚደረግ ሲሆን÷ ሊቢያዊው ዳኛ ኢብራሂም ሙታዝ ጨዋታውን በዋና ዳኝነት እንደሚመሩት ተገልጿል፡፡
ባምላክ ተሰማ ከዚህ በፊት በ2017 በአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊገ ለፍፃሜ የደረሱትን አል አህሊ እና ዋይዳድ ካዛብላንካ በዋና ዳኛነት መርተው እንደነበር ይታወሳል፡፡
ኢንተርናሽናል አርቢትሩ የግብፁ ክለብ አል አህሊ ካደርጋቸው ጨዋታዎች አስሩን በዋና ዳኝነት የመሩ ሲሆን÷ በአንፃሩ ከሞሮኮው ተወካይ ዋይዳድ ካዛብላንካ ካደረጋቸው ጨዋታ ውስጥ አራቱን በዋና ዳኝነት መርተዋል፡፡