Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ መኮንን ከቻይና ምክትል ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 18 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከቻይና ምክትል ፕሬዚዳንት ሃን ዠንግ ጋር ተወያዩ።
 
በውይይቱ ወቅት አቶ ደመቀ በኢትዮጵያ ሰላምን ወደነበረበት ለመመለስ እና ለችግሮች ምላሽ ለመስጠት ለሚደረገው ጥረት ቻይና ለምታደርገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።
 
አያይዘውም ኢትዮጵያ በቻይና በሚተገተበሩ ጠቃሚ ውጥኖች ላይ በንቃት የመሳተፍ ፍላጎት እንዳላት ተናግረዋል።
 
ኢትዮጵያ ለምታልመው የእድገት ግብ ቻይናን እንደ ዋነኛ አጋሯ ትመለከታታለች ያሉት አቶ ደመቀ፥ ቻይና ከጦርነት በኋላ በሚደረጉ የመልሶ ግንባታ እና ኢኮኖሚ የምታደርገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.