የሀገር ውስጥ ዜና

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የግብርና እና የሳይንስ አውደ ርዕይን ጎበኙ

By Feven Bishaw

May 26, 2023

 

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በሳይንስ ሙዚየም የተከፈተውን የግብርና እና የሳይንስ አውደ ርዕይ ጎብኝተዋል።

‘ከቤተ ሙከራ እስከ አዝመራ’ በሚል መሪ ቃል ግብርና ሚኒስቴር ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የግብርና ሳይንስ አውደ ርዕይ ለዕይታ ክፍት ከሆነ ሳምንታትን አስቆጥሯል።

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በዛሬው ዕለት አውደ ርዕዩን ጎብኝተዋል።

በአውደ ርዕዩ የፌዴራል እና የክልል ግብርና ቢሮ ስራዎች እየቀረቡ ሲሆን÷ በዛሬው ዕለት የደቡብ ክልል የግብርና ዘርፍ ልማት እንቅስቃሴዎች ለዕይታ መቅረባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።