Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮ ቴሌኮም በአዲስ አባባ ዩኒቨርሲቲ ስማርት የመማሪያ ክፍል አስጀመረ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮ ቴሌኮም ለኢትዮጵያ ፈር ቀዳጅ የሆነውን ስማርት የመማሪያ ክፍል ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አራት ኪሎ ግቢ በመገንባት ዛሬ ሥራ ላይ እንዲውል አድርጓል፡፡

በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ(ፕ/ር)፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ጣሰው ወልደሃና(ፕ/ር)፣ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩን ጨምሮ ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

የስማርት የመማሪያ ክፍሉ የተለያዩ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች የተሟሉለት በመሆኑ የመማር ማስተማሩን ሂደት በቀላሉ ለማከናወን ያስችላል ነው የተባለው፡፡

በተለይም የትምህርት ተቋማት የትምህርት ዘርፍን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ዕውን ለማድረግ፣ የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል፣ የማስተማሪያ ወጪዎችን ለመቀነስ እና ለቤተሙከራ የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን ለመግዛት የሚውሉ ወጪዎችን ለመቀነስ ትልቅ አስተዋፅኦ እንዳለው ተጠቁሟል፡፡

የትምህርት መረጃዎችን በቀላሉ ለማግኘት እና የዲጂታል ቴክኖሎጂውን በሚጠቀሙ እና በማይጠቀሙ መካከል ያለውን ክፍተት ለማጥበብ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረውም ነው የተመላከተው፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም በትምህርት ዘርፉ ግንባር ቀደም ተዋናይ ከመሆኑም ባሻገር በሃገር አቀፍ ደረጃ የትምህርት ዘርፉን ለማሻሻል እና የዲጂታል ኢትዮጵያን ራዕይ እውን ለማድረግ የተያዘውን እቅድ ለማሳካት እየተከናወኑ የሚገኙ ሁለገብ ሀገራዊ ጥረቶች ይበልጥ ፍሬ እንዲያፈሩ የበኩሉን ድርሻ በመወጣት ላይ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በአዲሱ ሙሉነህ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.