Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከብክለት ነጻ የሆነ የጭነት አገልግሎት በመስጠት የአፍሪካ የአመቱ አየር መንገድ ሽልማትን አሸነፈ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 19 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከብክለት ነጻ የሆነ የጭነት አገልግሎት በመስጠት የአፍሪካ የአመቱ አየር መንገድ ሽልማትን አሸነፈ።

 

አየር መንገዱ በቱርክ ኢስታንቡል በዘርፉ የተሰማሩ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች፣ ተገልጋዮች እና መራጮች በሰጡት ድምጽ ነው አሸናፊ የሆነው።

 

በአጋሮች እና ተገልጋዮች በሚሰጠው የዘርፉ የጭነት አገልግሎት ቀዳሚ ሆኖ በመመረጡ የተሰማውን ደስታ ገልጿል።

 

በቀጣይም በጭነት አገልግሎት ያለውን ቀዳሚ ሚና እና ለደንበኞቹ የሚሰጠውን ውጤታማ አገልግሎት  እንደሚያስቀጥልም አስታውቋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.