ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ የተ.መ.ድ የሰዓብዊ ድጋፍ አስተባባሪ በፈተና ወቅት ለሰጡት አመራር ምስጋና አቀረቡ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ ድጋፍ አስተባባሪ ካትሪን ሱዚ (ዶ/ር) ለኢትዮጵያ በፈተና ወቅት ለሰጡት አመራርና ሰብዓዊ ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ፕሬዚደንቷ የአገልግሎት ጊዜያቸውን የጨረሱትን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ ድጋፍ አስተባባሪ ካትሪን ሱዚ (ዶ/ር)ን በዛሬው እለት አሰናብተዋል፡፡
ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ÷ ሱዚ (ዶ/ር ) ኢትዮጵያ በከፍተኛ ሁኔታ በተፈተነችበት ወቅት የተመድ ቡድንን በማስተባበር ላሳዩት አመራር ነው ምስጋና ያቀረቡት።
በተጨማሪም÷ የተመድ ተልዕኮ በማንኛውም ሁኔታ ለተመደቡበት አገር ሕዝብ የመድረስ ተልዕኳቸውን ለተወጡ ኢትዮጵያውያንና የውጭ አገር ዜጎች እንዲሁም የድርጅቱ አባላት ምስጋና አቀርባለሁ ሲሉ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡