Fana: At a Speed of Life!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከዋሺንግተን ዲሲ ከንቲባ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የከተሞችን ሁለትዮሽ ግንኙነት በማጠናከር ዙሪያ ከዋሺንግተን ዲሲ ከንቲባ ሙሪዬል ቦውዘር ጋር መክረዋል፡፡

በውይይታቸውም÷የአዲስ አበባ እና የዋሺንግተን ዲሲ ከተሞች የእህትማማችነት ስምምነት ወደ ተግባር እንዲለወጥ ለማስቻል መምከራቸውን ከንቲባ አዳነች በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ ገልጸዋል፡፡

በተለይም በመንግስት እና የግል አጋርነት በሚገነቡ የተቀናጁ የልማት ፕሮጀክቶች የነዋሪዎችን ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ከተማን መልሶ በማልማት፣ የተሻለ ገቢ አሰባሰብ የውሃ ማከም ላይ በጋራ ለመስራት ተወያይተናል ብለዋል፡፡

በተጨማሪም በትራንስፖርት፣ በዙሪያ ካሉ ከተሞች ጋር የልማት ስራዎች በማቀናጀት ላይ ልምዶችን በመቀመር እና በመለዋወጥ በትብብር ለመስራት ስምምነት ላይ መድረሳቸውንም ገልጸዋል፡፡

እንዲሁም ከተማን መልሶ የማልማት እና መልሶ የመጠቀም ስራዎችንም መጎብኘታቸውን ከንቲባዋ ጠቅሰዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.