የሀገር ውስጥ ዜና

በሲዳማ ክልል ለመከላከያ ሰራዊት የድጋፍ ሰልፍ ተካሄደ

By Mikias Ayele

May 28, 2023

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሲዳማ ክልል  ዜጎች ለመከላከያ ሠራዊት ያላቸውን ድጋፍ በታላቅ ሠላማዊ ሰልፍ ገልፀዋል።

በሀዋሳ ከተማ ሰልፉ የተካሄደ ሲሆን ÷ከከተማዋ የተለያዩ ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ  ነዋሪዎች  ለመከላከያ ሰራዊቱ ድጋፋቸውን ገልፀዋል ፡፡

ከህብረ ብሄራዊ ሰራዊታችን ላይ እጃችሁን አንሱ፣እሱ ሞቶ እኛን ያዳነንን ሰራዊት ማጠልሸት ይቁምና ሌሎች ሰልፈኞቹ  እያሰሙ ከሚገኙት መፈክር ይጠቀሳል፡፡