በኦሮሚያ ክልል ለመከላከያ ሰራዊት የድጋፍ ሰልፍ ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል “መከላከያ ስራዊታችን ኢትዮጵያዊነታችን” በሚል መሪ ቃል ለመከላከያ ሰራዊት የድጋፍ ሰልፍ ተካሄደ፡፡
ሰልፉ በክልሉ በሸገር ከተማ፣ ጅማ፣አዳማ፣ሻሸመኔ፣አምቦ፣ቢሾፍቱና በሌሎች ከተሞች ተካሂዷል፡፡
እየተካሄደ በሚገኘው ሰልፍ “መከላከያ ሰራዊታችን አንድነታችንን ይገነባል፤ ፅንፈኞች ያፍራሉ” ፤”የኢትዮጵያዊነታችን አርማ የሆነውን መከላከያ ሰራዊት በመተንኮስ የስልጣን ፍላጎትን ማሳካት አይቻልም”የሚሉና ሌሎች መልዕክቶችም እየተላለፉ ነው።
በሰልፉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችን ጨምሮ የዕምነት አባቶች ፣አባገዳዎች፣ ሀዳ ሲንቄዎች እና የከተማዋ ነዋሪዎች ተገኝተዋል።
በወንድሙ አዱኛ