Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ክልል “መከላከያ ሠራዊታችን ኢትዮጵያዊነታችን” በሚል መሪ ቃል የድጋፍ ሰልፍ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል “መከላከያ ሠራዊታችን ኢትዮጵያዊነታችን” በሚል መሪ ቃል የድጋፍ ሰልፍ ከማለዳው ጀምሮ ተካሂዷል፡፡

በአርባ ምንጭ እና ዲላ ከተማ በተካሄደ  ሰልፍ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እየተሳተፉ ሲሆን÷ አለኝታችን በሆነው ሠራዊታችን ላይ ምላሳቸውን የሚዘረጉ ጽንፈኞች በህግ ይጠየቁ፤መከላከያ ሠራዊታችንን ተቀላቅለን ኢትዮጵያችንን እናጸናለን፤መከላከያችን አንድነታችንን ይገነባል ጽንፈኞች ያፍራሉ የሚሉ መፈክሮች ተሰምተዋል፡፡

እንዲሁም ብሔሩ አገሩ የሆነን ሠራዊት መነካካት የለየለት ጠላትነት ነው፤ መከላከያችን እንወድሀለን እናከብርሀለን ሁሌም እንደግፍሀለን፤የህዝቦችን አንድነትና ወንድማማችነት የሚሸረሽሩ ጽንፈኞች በህግ ይጠየቁልን፤ብረ ብሔራዊ ፌደራሊዝም ለኢትዮጵያ አንድነት ዋስትና ነው፤ጽንፈኞች የፖለቲካ ነጋዴ እንጂ የማንም ብሔር ወኪል አይደሉም የሚሉም ከመፈክሮቹ ውስጥ የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.