Fana: At a Speed of Life!

በሶማሌ ክልል ለመከላከያ ሰራዊት የድጋፍ ሰልፍ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል ለመከላከያ ሰራዊት የድጋፍ ሰልፍ ተካሂዷል።

በጅግጅጋ ከተማ በተካሄደ በሚገኘው የድጋፍ ሰልፍ በከተማዋ ከሁሉም ክፍለከተሞች የተውጣጡ ዜጎች በጅግጅጋ ስታዲየም ተገኝተው ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ያላቸውን ድጋፍ ገልፀዋል።

ሰልፈኞቹ “ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ” በሚል መርህ ህይወቱን ሰውቶ ሀገር የሚያቀናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት “አርማችንና መመኪያችን” የሚሉ መፈክሮችን አሰምተዋል፡፡

በተጨማም መከላከያችን አንድነታችንን ይገነባል ፅንፈኞች ያፍራሉና ብሔሩ አገሩ የሆነን ሠራዊት መነካካት የለየለት ጠላትነት ነው ” የሚሉ መፈክሮችም በሰልፉ ተስተጋብተዋል።

በዓለምሰገድ አሳዬ

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.