Fana: At a Speed of Life!

የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር በጅግጅጋ ከተማ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር በዛሬው ዕለት በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ ተካሂዷል፡፡

በኢትዮጵያ አትሌቶች ማህበር እና በጅግጅጋ ከተማ አስተዳደር የተዘጋጀው ውድድሩ÷”ለሀገር ሰላም እሮጣለሁ” በሚል መሪ ቃል ነው የተካሄደው፡፡

በመርሐ ግብሩ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ቀጄላ መርዳሳ፣ የሶማሌ ክልል ም/ርዕሰ መስተዳድር ኢብራህም ኡሰማንና የአትሌቲክስ ፌድሬሽን ፕሬዚዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉን ጨምሮ ሌሎች አንግዶች ተገኝተዋል፡፡

በጎዳና ላይ ሩጫው የሶማሌ ክልልን ጨምሮ ከሀገሪቱ ከተለያዩ የግልና የመንግስት ተቋማት የተውጣጡ ከ70 በላይ አትሌቶች ተሳትፈዋል።

በውድድሩ ከ1ኛ እስከ 3ኛ ደረጃ ለወጡ አትሌቶች የማበረታቻ የገንዘብና የሜዳሊያ ሽልማት የተበረከተላቸው መሆኑን የሶማሌ ክልል ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.