Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ የጉዋንዡ ከተማን ከኢትዮጵያ ከተሞች ጋር ማስተሳሰር እንደሚያስፈልግ ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) መንግሥት የጉዋንዡ ከተማን ከኢትዮጵያ ከተሞች ጋር የማጎዳኘት ፍላጎት እንዳለው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ገልጸዋል።
በቻይና ጉብኝት እያደረጉ ያሉት አቶ ደመቀ የጉዋንዡ ከተማ ከንቲባ ጉዎ ዮንግሃንግ ባደረጉላቸው የእንኳን ደህና መጡ ግብዣ ላይ እንደተናገሩት÷ የሕዝብ ለሕዝብ ትሥሥሩ የበለጠ እንዲጠናከር በጉዋንዡ እና በኢትዮጵያ ከተሞች ማካከል ትስስር መፍጠር ጠቃሚ ነው ብለዋል፡፡
የጉዋንዡ ከተማ 16 ሚሊየን ነዋሪ ያላት ስትሆነ የቻይና የቢዝነስ መናኸሪያ የሆነው ጓንዶንግ ግዛት ዋና ከተማ መሆኗ ተገልጿል፡፡
የከተማዋ ከንቲባ የኢትዮጵያ የወጪ ምርቶች መዳረሻቸውን በጉዋንዡ እንዲያደርጉ ለኢትዮጵያ አምራቾች ጥሪ ማቅረባቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ጉዋንዡ በመብረር ሁለቱን ሀገራት ብቻ ሳይሆን ቻይና እና አፍሪካን አንዳስተሳሰረ ጠቅሰው÷ በተለይም የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት በጉዋንዡ የሚያደርገውን በረራ ባለማቋረጡ አመስግነዋል።
አቶ ደመቀ በጉዋንዡ ቆይታቸው የኤሌክትሮኒክስ፣ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጅ እና ከኃይል ማመንጫ ጋር የተያያዙ ኩባንያዎችን በመጎብኘት በኢትዮጵያ እንዲሰማሩ ጋብዘዋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.