Fana: At a Speed of Life!

አብርሃም በላይ (ዶ/ር) ለመከላከያ ሠራዊት ለደተረገው ድጋፍ አመሰገኑ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የመከላከያ ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር) በተለያዩ አከባቢዎች ለጀግናው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ለደተረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።
 
ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ለሠራዊቱ የተደረገው ከፍተኛ የድጋፍ ሰልፍ፣ በተቀሩት የሀገሪቱ ክፍሎች ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን አንስተዋል፡፡
 
ድጋፉ ሀገራዊ ሰላም እና መረጋጋትን ለማስፋት የተጀመሩ ጥረቶችን ሰፊ ሕዝባዊ ቅቡልነት ከወዲሁ የሚያመላክት እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡
 
“መከላከያ ሰራዊት ሀገር እና ሕዝብ በሰላም እንዲኖር ሌት ተቀን የሚሠራ፣ የሀገር ሉዓላዊነት እና የዜጎች ደኅንነት እንዲረጋገጥ መተኪያ የሌላትን ሕይወቱን እየሰጠ ያለ ዋስናችን ነው” ሲሉም አውስተዋል።
 
“ሠራዊቱን ከውጭ ሆነ ከውስጥ ሆነው ስሙን ለማጠልሸት እና ሀገር የማተራመስ አጀንዳ የወሰዱ አካላት፣ የሚያደርጉት የጥፋት እንቅስቃሴ ከሕዝባችን ጋር ሆነን እያመከንን የኢትዮጵያን ብልፅግና እውን እናደርጋለንም” ብለዋል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.