Fana: At a Speed of Life!

በፕሪሚየር ሊጉ ድሬደዋ ከተማ ፋሲል ከነማን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 26ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ድሬደዋ ከተማ ፋሲል ከነማን አሸንፏል፡፡

ቀን 9 ሰዓት ላይ በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ድሬደዋ ከተማ ፋሲል ከነማ 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

የድሬደዋ ከተማን የማሸነፊያ ግቦች መሃመድ አብዱላጢፍ በ22ኛው እና ቻርልስ ሙሲጌ በ82 ደቃቂ ላይ አስቆጥረዋል፡፡

ፋሲል ከነማን ከሽንፈት ያልታደገችዋን ብቸኛ ግብ ደግሞ ሽመክት ጉግሳ በ25ኛው ደቃቂ ላይ አስቆጥሯል፡፡

12 ሰዓት ላይ ተጀምሮ የነበረው የሲዳማ ቡና እና ወላይታ ድቻ ጨዋታ እስከ እረፍት ያለምንም ግብ የተጠናቀቀ ቢሆንም በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት ተቋርጧል፡፡

ቀጣይ ጨዋታውም ከቆመበት ደቂቃ ሁለተኛው አጋማሽ ነገ ግንቦት 21ቀን2015 ዓ.ም በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ከቀኑ 7 ሰዓት ላይ እንዲደረግ መወሰኑን የሊግ ካንፓኒው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.