Fana: At a Speed of Life!

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሊድስ ዩናይትድ እና ሌሲስተር ሲቲ ወደ ታችኛው ሊግ ወረዱ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሊድስ ዩናይትድ እና ሌሲስተር ሲቲ ወደ ታችኛው ሊግ ወርደዋል።

በሊጉ የመጨረሻ ሳምንት መርሐ ግብር ሌሲስተር ከዌስትሀም ጋር ተጫውቶ 2 ለ 1 ሲያሸንፍ ሊድስ በቶተንሀም 4 ለ 1 ተሸንፏል።

በሜዳው ከበርንማውዝ የተጫወተው ኤቨርተን ደግሞ 1 ለ 0 አሸንፏል።

ውጤቱን ተከትሎም ኤቨርተን በመጨረሻው ሳምንት በፕሪሚየር ሊጉ መቆየቱን አረጋግጧል።

በአንጻሩ ሊድስ እና ሌሲስተር ቀደም ብሎ መውረዱን ያረጋገጠውን ሳውዝሃምተንን ተከትለው ወደ ታችኛው ሊግ ወርደዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.