Fana: At a Speed of Life!

በምዕራብ ሸዋ ዞን አንዲት በቅሎ መውለዷ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ባኮ ቲቤ ወረዳ አንዲት በቅሎ መውለዷ ተነግሯል፡፡
 
የበቅሎዋ ባለቤት አቶ ብርሃኑ ተምትሜ ÷ በ2014 በቅሎዋን እንደገዟት እና ለማጓጓዣ አገልግሎት ሲጠቀሙባት መቆየታቸውን ተናግረዋል።
 
ነገር ግን የበቅሎዋ ሆድ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱን እንዳአስተዋሉ እና ግንቦት 15 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 5፡30 ላይ እንደወለደች አረጋግጠዋል፡፡
 
የበቅሎዋ መውለድ ክስተት እንዳስገረማቸው አንስተው÷ ውርንጭላው አሁን ላይ በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኝ ጠቁመዋል፡፡
 
በባኮ ቲቤ ወረዳ ግብርና ጽ/ ቤት የእንስሳት ሐኪም የሆኑት ዶክተር ለማ አያላ÷በቅሎ ሲወልድ አይተው እንደማያውቁ እና ክስተቱ እንግዳ እንደሆነባቸው ገልፀዋል፡፡
 
ባለሙያው በቅሎ አትወልድም የሚለው እሳቤ በሳይንስ እና በባህላዊ መንገድ የታመነበት ጉዳይ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
 
ይሁን እንጂ አልፎ አልፎ ከአንድ ሚሊየን በቅሎዎች አንዳቸው ሊወልዱ እንደሚችሉ መግለጻቸውን የወረዳው ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.